H
ከውክፔዲያ
| የላቲን አልፋቤት | ||||||
|---|---|---|---|---|---|---|
| A | B | C | D | E | F | |
| G | H | I | J | K | L | M |
| N | O | P | Q | R | S | T |
| U | V | W | X | Y | Z | |
| ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
| Þ... | ||||||
H / h በላቲን አልፋቤት ስምንተኛው ፊደል ነው። በእንግሊዝኛ የፊደሉ ስም አጠራር /ኧይች/ ቢሆንም፣ የተናባቢው ድምጽ /ህ/ ያሰማል።
| ግብፅኛ ሰፐአት |
ቅድመ ሴማዊ ሔት |
የፊንቄ ጽሕፈት ሔት |
የግሪክ ጽሕፈት ሄታ/ኤታ |
ኤትሩስካዊ H |
ላቲን H |
||
|---|---|---|---|---|---|---|---|
|
![]() |
የ«H» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ሔት» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአጥር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ሔት ድምጽ እንደ ተናባቢ («ሕ») ሲሆን በግሪክ አልፋቤት እንዲሁም ሄታ ለ «ህ» ተጠቀመ። ከ400 ዓክልበ. ግድም በኋላ ግን ይህ ምልክት (Η η) የአናባቢ ድምጽ «ኤ» ለማመልከት ይጠቅም ጀመር። ሆኖም በጥንታዊ ጣልያን አልፋቤቶች እንደ ኤትሩስካዊ አልፋቤት እና ላቲን አልፋቤት፣ «H» ተናባቢውን «ህ» በመወክል ቆየ።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ሐ» («ሐውት») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ሔት» ስለ መጣ፣ የላቲን «H» ዘመድ ሊባል ይችላል።
